የራስዎን አኳፖኒክስ ይጀምሩ

የራስዎን የግል ንግድ ሥራ ለመጀመር የሚአስፈልጉ ነገሮች

1 የራስዎን ይጀምሩ

አኳፖኒክስ በኢትዮጵያ አሣ እና አትክልት ለማምረት ጥሩ አጋጣሚ ፈጥሯል፡፡  ለአለፉት ሁለት ዓመታት አኳፖኒክስ በኢትዮጵያ የማላመድ ጥናት በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል፡፡  ይህ ድረገፅ ለአኳፖኒክስ እርሻ ጀማሪዎች የንግድ ሥራ ሞዴል እና የአሠራር ፅንሰ ሐሳብን በተመለከተ መረጃ ያቀርባል፡፡  አኳፖኒክስ በኢትዮጵያ በተለያየ መጠን ሊዘጋጅ ይችላል፡፡  በኢትዮጵያ የዚህን እርሻ ውጤታማነት ለማወቅ ከ24 እስከ 3000 ካ.ሜ ቦታ ላይ ተሞክሯል፡፡  24 ካ.ሜ ቦታ ከ24000 እና ከ30000 ብር በሆነ አነስተኛ ወጪ ሊገነባ ይችላል፡፡  በዚህም መሠረት በ24 ካ.ሜ ቦታ ላይ የተመረተ አትክልት ለ6 ቤተሠብ በበቂ ሁኔታ ይመግባል፡፡  ይህ ገፅ እርስዎ እኳፖኒክስ እርሻ እንዴት መጀመር እንዳለብዎት መረጃ ያቀርብሎታል፡፡

2 የገብያ ጥናት

በማንኛው ንግድ ሥራ ላይ ብዙ ሐብት ከመፍሰሱ በፊት የገብያ አዋጭነት ጥናት መካሔድ አለበት፡፡  ለአኳፖኒክስ የገበያ ፍላጐት፣ የመሸጫ ዋጋ እና ጥራትን በተመለከተ በበቂ ሁኔታ ማወቅ ተገቢ ነው፡፡  አኳፖኒክስ ለመጀመር የሚአስፈልገውን ከፍተኛ መዋለ ንዋይ በአጭር ግዜ ለመመለስ፣ የዚህ ንግድ ሥራ ሞዴል መከተል ተገቢ ነው፡፡  ቱሪስት በሚአዘወትራቸው ትላልቅ ከተሞች በአኳፖኒክስ ዘዴ የተመረተ አሣ እና አትክልት ከፍተኛ ዋጋ ሊአወጣ ይችላል ተፈጥሮአዊ (ኦርጋኒክ) ምርት  መሆናቸው ከተዋወቀ፡፡

3 ግንባታ

የአኳፖኒክስ ቦታ በአንድ ከተማ ውስጥ ሊገኙ በሚችሉ ቁሶች ሊገነባ ይችላል፡፡  አዲስ አበባ ብቻ የሚገኙ ቁሶች የውሀ መግፍያ ማሽን በውሀ ውስጥ የአየር መሙያ ማሽን እና የመሬት ንጣፍ ኘላስቲክ ናቸው፡፡  ከታች የተቀመጠው ስዕል የ24 ካ.ሜ አኳፖኒክስ አቀማመጥ ወይም አቀያየስ ነው፡፡  ተጨማሪ መረጃ የአኳፖኒክስ አያያዝ (አመራር) ድረ ገፅን ይመልከቱ፡፡  ግንባታው  የተለያዩ ቁሳቁሶች ከተገኙ በሁለት ቀን ውስጥ ይጠናቀቃል፡፡

የ24 ካ.ሜ ዋና ዋና ክፍሎች (አካላት)

  1. ሁለት አይቢሲ የአሣ ታንከር
  2. ከ3 እስከ 4ካ.ሜ የሚሆን ቀይ ኮረኮንች የእሳተገሞራ አሸዋ
  3. ውሀ የሚሠበስብ መለስተኛ ታንከር

15 በእየ 25 ሴ.ሜ የተበሳ ፒቪሲ (11ዐ ሚ.ሜ)  ቱቦ

 

Aquaponics material providers in Ethiopia

4 ሙዋለንዋይ ፍሰት እና ትግበራ

ለሦስት የተለያየ መጠን ላላቸው አኳፖኒክስ የሚአስፈልጉ ዝርዝር ቁስ አካላት ከእነዋጋቸው ተዘርዝረዋል (ተቀምጧል)፡፡  በ2ዐ1ዐ ዓ.ም የተሠበሠበ የዋጋ ዝርዝር በኤክሴል ፋይል ለማግኘት እዚህ ይጫኑ፡፡  የተለያዩ የንግድ ሥራ ጉዳዮችን ለማየት ከፈለጉ በስዕሉ ላይ ያለውን ቀስት መሳይ ምልክት ይጠቀሙ፡፡

 

5 የንግድ ሥራ ዕቅድ ማዘጋጀት

ከታች የተቀመጠው ሠንጠረዥ የአኳፖኒክስ ንግድ ስራ ሞዴልን በሦስት የተለያዩ ደረጃዎችን ያሣያል፡፡  እርስዎ በኤክሴል የተለያዩ የዋጋ ዝርዝር ማዘጋጀት ከፈለጉ ይህን ይጫኑ፡፡  የተለያዩ የንግድ ሥራ ጉዳዮችን ማየት ከፈለጉ በስዕሉ ላይ ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ፡፡

 

6 ግብዓት

አኳፖኒክስ ውጤታማ እንዲሆን የተለያዩ ግበአቶች ያስፈልጋሉ፡፡  እነዚህን ሁሉ ግብዓቶች ማሟላት ካልቻሉ፣ ሃይድሮፖኒክስ የተሻለ ምርጫ ነው፡፡  አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡

የአሣ ምግብ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ እኛን ያግኙ፡፡  ማ ኮጅስ (Alema-Koudijs) ከ1000 ኪ.ግ ጀምሮ ጥሪቱን የጠበቀ የአሣ ምግብ ያቀርባል፡፡
(ትላፒያ) ፈንገርሊንግስ ፡- ተጨማሪ ከፈለጉ እና ያግኙ
ዘር፡-  በብዛት በእርሻ መጋዝኖች ይገኛል፡፡
ውሀ፡–  የቧንቧ ውሀ እጅግ በጣም ጥሩ ነው፡፡  ጭቃ፣ አሸዋ እና ጠጠር ነገሮችን ማጣራት ከቻልን ገፀ ምድር ውሀም ጥሩ ነው፡፡  (ሁሌም የሚችሉ ከሆነ የውሀውን ጥራት ከመጠቀምዎ በፊት ያረጋግጡ!)
ኤሌክትሪሲቲ  ሁሉም የአኳፖኒክስ 24 ሰዓት ኤሌክትሪሲቲ ይፈልጋል፡፡ ከ3-4 ሰዓታት ድረስ ሊቆይ የሚችል የኤሌክትሪሲቲ ሓይል መቆራረጥ ተቀባይነት አለው፡፡  የኃይል መቆራረጡ ከ4 ሰዓት በላይ የሚቆይ ከሆነ ባትሪ መጠቀም  አሣዎች በኤሬተር አማካኝነት ኦክስጅን እንዲአገኙ ስለሚአግዝ በጣም ጥሩ ነው፡፡
ተባይን መቆጣጠሪያ ስልት፡- የተባይ ቁጥጥርን በተመለከተ Aquaponics Management ድረገፅን ይጐብኙ፡፡

 

 

7 ምርት

 

7 ምርት

ቲማቲም ፣ ቀይ ሽንኩርት ፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ጥቅል ጐመን ቆስጣ፣ ቃሪያ እና ድንች በብዛት ጥቅም ላይ የዋሉ አትክልት ናቸው፡፡  ከመሠረታዊ አትክልቶች በተጨማሪ፣ ልዩ የአትክልት ዝርያዎች በጥቂት የአትክልት መደብሮች ይገኛሉ፡፡  እነዚህ ዝርያዎች ላቅ ያለ ሀብት ባላቸው ቤተሰቦች፣ ሆቴሉች እና ምግብ ቤቶች ሊገኙ ይችላሉ፡፡  ከእነዚህ መካከል ጐመን፤ቆስጣ፣ ቼሪ ቲማቲም፣ የአበባ ጐመን ፣ ዚኩኒ፣ የፈረንጅ ጐመን፣ የፈረንጅ ዱባ፣ ቤል ቃሪያ፣ የቻይና ጐመን፣ ጥሬውን የሚበላ አትክልት፣ ሲሌሪ፣ የአይስ በርግ ሰላጣ፣ ባሮ ሽንኩርት እና የሩኮላ ሰላጣ ለምሣሌነት ይጠቀሳሉ፡፡  ከነዚህ ውስጥ የፈረንጅ ዱባ፡ ሰላጣ፡ የቻይና ጐመን እና ዝኩኑ በሆቴሎች በብዛት ይፈለጋሉ፡፡  አንዳንድ ሆቴል እና ምግብ በቶች በብዛት የማይገኙትን የተለያዩ የዕፅዋት ባህሪ ያላቸው አትክልቶችን ፣ ባዝል፣ ሚንት ፣ ድምብላል ቅጠል፣ የምግብ ማጣፈጫ ተክል፣ እና በሶብላ ሲፈልጉ ይስተዋላል፡፡  ከነዚህ መካከል የትኛው ዕፅዋት በአኳፖኒክስ ዘዴ ሊመረት እንደሚችል ምርምር ተካሂዷል፡፡

በአኳፖኒክስ ዘዴ ሊመረቱ የሚችሉት ሎሎ ሮሶ እና ሎሎ ቢያንኮ ገብያ ላይ በብዛት ይፈለጋሉ፡፡  እየአንዳዳቸው፥ አንድ ኪ.ግ  6ዐ ብር ያወጣል፡፡

በእሳተ ገሞራ ጠጠር ላይ የፈረንጅ ዱባ እና ዝኩኒ በአኳፖኒክስ አመራረት ጥሩ ሁነው ይበቅላሉ፡፡  የአንድ ኪ.ግ ዝኩኒ ዋጋ 35 ብር ሲሆን የአን ኪ.ግ የፈረንጅ ዱባ ዋጋ ደግሞ 5ዐ ብር ሊደርስ ይችላል፡፡

 

 

 

This post is also available in: en