አኳፖኒክስ ምንድ ነው?

አኳፖኒክስ እንዴት ይሠራል? ኢትዮጵያዊያን ከአኳቦኒክስ እንዴት ይጠቀማሉ?

የአኳፖኒክስ ገለፃ
አኳፖኒክስ አትክልትና አሣን በአንድ ላይ የማምረት ዘዴ ነው፡፡  አትክልቶች በአፈር ፈንታ ከውሀው ውስጥ ያለውን ንጥረ ነገር በመጠቀም የሚአድጉ ሲሆን የአሣው ቦታ ከአትክልት ማደጊያው ጋር በዝግ ቱቦ የተገናኘ ነው፡፡  በውሀ ውስጥ የሚኖሩ ደቂቀ አካላት /ባክቴሪያ/ አሣው ያመረተውን መርዛማ አሞኒያ ወደ አትክልት ሊጠቀሙበት ወደሚችለው ናይትሬት ይቀይራሉ፡፡  አትክልትን በውሀው ውስጥ ያለውን ለዕድገት በሚጠቀሙበት ስዓት፣ ውሀውን በማጣራት ተመልሶ ለአሣዎች ጥቅም እንዲውል ያደርጉታል፡፡

ምንም እንኳ የአኳፖኒክስ ፅንሰ ሐሳብ ለአንድ ክፍለ ዘመን የቆዩ ቢሆንም፣ አዲስ የአኳፖኒክስ ፍላጐት ያደገው በአለፈው አሥርት ዓመታት ነው፡፡  ይህ የማምረቻ ዘዴ በቻይና የሩውዝ እርሻ አፈርን ለም ለማድረግ ይጠቀሙበታል፡፡

በአፍሪካ የአኳፖኒክስ እምቅ ሐብት
በአለም አቀፍ ደረጀ በቂና ጤናማ ምግብ ቀጣይነት ባለው መንገድ ማምረት አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል፡፡  አኳፖኒክስ ይህንን ችግር ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡  በአኳፖኒክስ የተመረተ ምግብ የቫይታሚን እና ኘሮቲን ይዘት ከፍተኛ ስለሆነ ምግብን ለማበልፀግ ያግዛል፡፡  ከዚህ በተጨማሪ የአኳፖኒክስ የሥራ እድል ይፈጥራል፡፡ ገቢም ያስገኛል፡  አኳፖኒክስ የውሀ ዕጥረት፣ የእርሻ መሬት እጥረት፣ እና የእርሻ ግብዓት እጥረት ባለባቸው በማደግ ላይ ላሉ አገሮች እጅግ በጣም ጠቃሚ እና ምቹ የእርሻ ዘዴ ነው፡፡

  • 8.5 እጥፍ ከመደበኛው እርሻ ውሀን ይቆጥባል፡፡
  • በካ.ሜ የሚሰጠው ምርት ከመደበኛ እርሻ ይልቃል፡፡
  • የተለያዩ የኬሚካል ግባዓቶችን ስለማይጠቀም አኳፖኒክስ ተፈጥሮአዊ (ኦረጋኒክ) አስተሪረስ ዘዴ ነው፡፡
  • የተመጣጠነ ምግብ እንድናገኝ የሚአግዙትን አትክልት እና አሣ በአንድ ላየ እንድናመርት ያደርጋል፡፡
  • በመጠን እና ውስብስብነት በተመለከተ ከትናንሽ የቤት ውስጥ እርሻ እስከ ትላልቅ ሄክታር እርሻ ድረስ ሊለያይ ይችላሉ፡፡
  • ለም አፈር ስለማያስፈልግ፣ ምቹ መደበኛ እርሻ በሌለበት ቦታ ላይ ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡

 

አኳፖኒክስ በኢትዮጵያ
ዛሬ ላየ ዜጐች የአኳፖኒክስ እርሻ  እንዲጀምሩ ለማስቻል በኢትዮጵያ በሦስት ክልሎች የተለያዩ የአኳፖኒክስ ስርዓት ተመስርቷል፡፡

ሸዋሮቢት: 8 የስራ ዕድል ፈጣሪዎች በ24 ካ.ሜ ላይ ለእያንዳንዱ
መትሐራ: የወጣችን የህብረት ሥራ ማህበር በ3ዐዐ0 ካ.ሜ ላይ
ሐዋሳ: 8 የስራ ዕድል ፈጠራዎች በ12 ካ.ሜ ላይ ለእያንዳንዱ

ሁሉም የስራ ዕድል ባለቤቶች ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ (ኢትዮጵያ)፥ ዋገንገን ዩኒቨርስቲ (ኔዘርላንድ)፥ቲጂኤስ የንግድ እና የልማት አጋር በተገኘ ድጋፍ የአኳፖኒክስ እና የንግድ ሥራ ፈጠራን በተመለከተ ሥልጠና ተሰጥቷቸዋል፡፡

የዚህ  ኘሮጀክት የምርምር ውጤት፥ ግለስቦች ጤናማ አሣ እና አትክልት በአኳፖኒክስ የማምረት ሥነ ዘዴን በመጠቀም እንዲአመረቱ የመረጃ ምንጭ ሆኖ ያገለግላል፡፡  የአኳፖኒክስ እርሻ ለመጀመር በኢትዮጵያ ጥሩ አጋጣሚ አለ፡፡  በኢትዮጵያ ከ1ዐ እስከ 2000 ካ.ሜ በሆነ ቦታ ላይ 400 እስከ 8000 ኪ.ግ የሚሆን አትክልት እና 100 እስከ 20000 ኪ.ግ የሚሆን ቆረሶ አሣ የማምረት አቅም አለ፡፡

This post is also available in: en