እንኳን ወደ አኳፖኒክስ ኢትዮጵያ ድረ ገፅ በደህና መጡ!  ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚከናወኑ የአኳፖኒክስ ስራ መረጃ ምንጭ

 

ከባህላዊ የመስኖ እርሻ ጋር ሲነፃፀር ፣ አኳፖኒክስ 8ዐ% ውሀ ይቆጥባል፡፡  አኳፖኒክስ ለም ባልሆነ መሬት ላይ ይተገበራል፡፡ ምክንያቱ ይህ የማምረቻ ዘዴ አፈር ስለማይጠቅም፡፡ ስለዚህ ፣ የእርሻ መሬት እጥረትን እና ድርቅን ለመከላከል ያግዛል፡፡  ይህን የንግድ ሞዴል ለመገምገም፣ የተለያዩ የግል ንግድ ሙያ ባለቤቶች (Entrepreneur)  ተመርጠዋል፡፡  ይህ ድረገፅ የተዘጋጀው የአኳፖኒክስ እርሻ እና ንግድን በተመለከተ፣ በተለያዩ ባለሙያዎች እና ተጠቃሚዎች መካከል እውቀትን እና ክህሎትን ለማጋራት ነው፡፡

 የአኳፖኒክስ ንግድ ሥራ ሞዴልን ለተጠቃሚዎች በማስተዋወቅ የሥራ ፈጠራን እናበረታታለን፡፡  ይህ የማምረቻ ዘዴ ጤናማ አትክልት/organic/  እና አሣን ኢትዮጵያ ውሥጥ በማምረት የሥራ አጥነትን ቁጥር ይቀንሳል፡፡

ዛሬ ላየ አኳፖኒክስ በሦስት ክልሎች ተመስርቷል፡፡

  1. ሸዋሮቢት: 8 የሥራ ፈጠራ ባለቤቶች በ12 ካ.ሜ ላይ
  2. መትሐራ: የወጣቶች ህብረት ሥራ ማህበር በ3ዐዐ ካ.ሜ ላይ
  3. ሐዋሳ:  8 የሥራ ፈጠራ ባለቤትን በ12 ካ.ሜ ላይ

This post is also available in: en